ለመሆኑ አንተ ማነህ

ይድረስ ለአቶ ጫኔ

ይድረስ ለአቶ ጫኔ

ውድ የኢትዮጵያ ዩዳዊያን ሆይ ይህ ግጥም የሚመለከተው በለፈ ሳምንት አንድ ንጽህ ይሁድ እኛ ነን እያለ በተለያዩ የመገኛ መስመሮች ላይ ሲፈክር የሰነበተውን አቶ ጫኔ የሚመለከት እንጂ ሌላ ግለሰብ የማይነካ መሆኑን ከወዲሁ አስታውቃለህ።

ለምሆኑ ማነህ?

ከመለሰ ስብሐት

ለምሆኑ ማነህ? እስቲ ልጠይቅህ?

ከጥንት ከጥዋቱ ከየት እንደመጣህ?

ይሁዲ ነህ አንተ ወይስ ከሌላ ዘር፣

እስቲ ማንነትህን ውጣና ተናገር።

እውነትን ሸፍነህ የማይሆን የተረክ፣

ዘራችሁ ዘሬ አይደል ብለህ ይተናገርክ።

አሁንም ተጠየቅ ለሆኑ ማነህ?

አንተ የእኛ ወንድም አንተ የእኛ ተላላ፣

እውነትን መሰለህ የነገሩህ ሁላ።

የሆነ ያልሆነ ነገር ነገሩህ፣

ሁሉን ተቀብለህ አንተም አወራህ።

ሰማህ የኔ ወንድም የጥንት የጥዋቱን፣

የቤተ እስራኤል ኑሮና ሕይወቱን፣

በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት እምነቱን።

እኔ እነግርሐለው አንተ ከዘነጋህ፣

ዝም ብለህ አዳምጥ ከማን እንደመጣህ።

ትመስላለህ አንተ ትቢት የወጠረህ፣

ያልነበርን ነበር ብለህ ታወራለህ።

ተመስገን ማለቱን ዘንግቷል ልብህ፣

ጦርነት ለመክፈት ትዘጋጃለህ።

ዘር ቆጠርኩ ያልከው የትኛውን ዘር ነው?

እኛ ብለህ ያልከው የትኛው እኛ ነው?

ከኢትዮጵያ የመጣ ሌላ ይሁዲ ነው?

ያወራኸው ወሬ መሠርት የለውም፣

የአንተን ይሁዲነት አያንጽባርቅም።

ምን ይሉህ መነኩሳት የቄሳውስት መሪ፣

ምን ይሉህ ቄሳውስት የሕዝቡ መካሪ፣

እንዴት ይታዘቡህ አዛውንቶቻችን፣

እያልክ ስታወራ ገደል መግባታችን፣

ስታወራ ወሬ የሽንብራ ፍሬ አለመሆናችን።

ይንገሩን እነሱ እውነተኛ ታሪኩን፣

ማን ይሁዲ እንድሆን፣ ማንኛው እንዳልሆን።

እባብ መርዝ ይረጫል በመጥፎ ምላሱ፣

ተግባሩ ነውና ሰውን ማነከሱ፣

የአንተና የእርሱ ተግባር አንድነት አላቸው፣

ሕዝብ የሚያለያዩ የሚያዋጉ ናቸው።

ቀደም የመጣ ነው፣ አሁን የመጣነው፣

በማለት የሕዝቡን አንድነት የሚበጠብጥ ነው።

ወጣቶች ተዋደው እንዳይዛመዱ፣

ጠላታችን ናቸው አልክ በገሐዱ።

ከምን አገኘኸው የእባብ መርዙነን፣

ከዘመድ ከዘመዱ የሚአፈጃውን።

ይህ አልበቃህ ብሎ ጠላቶች አልከን፣

ከአፍህ የወጣው ቃል ከአንተ አይጠብቅም፣

ከችግር በስተቀር መፍትሔ አይሰጥህም።

እኔን ካላመንከኝ የተናገርከውን፣

መለስ በልና ቃሉን መርምረው፣

ለልጅ ልጆቻችን የማይበጅ ነው።

አያት ቅማንቶችህ ከእኛ ግንድ ናቸው?

ወይስ ከሌላ ዘር ብቅ ያሉ ናቸው?

የንግግርህ መልዕክት እኔን አልገባኝም?

ጥሩ አርገህ አስረዳን ማነንነትህን።

ሐሳብህ ግትር ነው ከእውነት የራቀ፣

ውሸት ያነገበ የተንደላቀቀ።

ብቸኛ ይሁዲ እኔ ነኝ ማለትህ፣

ከእውነት የራቀ ነው ወንድሜ ልንገርህ።

ይገርማል!! እስቲ ልጠይቅህ ማነው ይሁዲው?

ሁለት ሽ ዘመን ሐማኖት ጠብቆ፣

የመጸሐፍ ቅዱስ ሕግን አሳውቆ፣

የኖረ ማን ይሆን ማንነቱን አውቆ።

ንብ የሌለው አውራ እንዳይሆን ሕዝባችን፣

ሁልጊዜ ጠባቂ እንዳይስት መንገዱን፣

መንኩሳትን ቄሳውስት ናቸው ዋልቶቻችን።

የሐይማኖት አባት ቄሳውስት ናቸው፣

ከጥንት ጀምሮ የታወቁ ናቸው።

አንተ እነሱ ብለህ ጨዋት ያወራህ፣

እኛ እንኳን እኛ ነን ለመሆኑ ማነህ?